HOME FOR SPIRITUAL MESSAGE BY FR ZEMENE DESTA

ታማኝ ሁን አደራ

ታማኝ ልጅ ይሉኃል መምህር አስታራቂ
የተዋሕዶ ልጅ የበጎች ጠባቂ
ተኩላ አይቶ የማይሸሽ ማተቡን አጥባቂ

ጥሪህን ተመልከት እንዳትዘናጋ
ቤተ ክርስቲያንህን ለማገልገል ትጋ
ነገር ግን ተጠንቀቅ
ከሰው አትጠብቅ የድካምህን ዋጋ

የወንጌል አዝማራ ስፋቱ ይደንቃል
ጽጌው ፍሬ ሲይዝ ለሁሉም ይበቃል

ይታይሃል ከሩቅ የተዋሕዶ አዝመራ
እሸቱ ያማረ ፍሬው የጎመራ
ይጠበቅብሃል ገና ብዙ ሥራ
ታጥቀህ ድረስለት ውጣ ተሠማራ
የኋላህን ሰብስብ የፊትህን ዝራ
ለወንጌል ተልዕኮ ታማኝ ሁን አደራ

ጉዞ ጀምረሃል በአባቶችህ መንገድ
ግራ ቀኝ እያየህ በጥንቃቄ ሄድ
በመንፈሳዊ ጎዞ በወንጌል ጎዳና
ቃል ሕይወት ይሁን ሥራህ ደማቅ ፋና
ዳሩ መሰናክል አይታጣምና
ሥራህን አከናውን በፍቅር በትህትና

በጣም ዝቅ አትበል እውቀት እንዳነሰው   
ይህ ዓለም አይወድም እንዲህ ዓይነቱን ሰው
በጣምም ከፍ አትበል ጣራ እንዳትነካ
This is America

ዱሮም የሰው ምክር ሁል ጊዜም አይሠራ
አንደኛው ወደ ቀኝ ሌላው ወደ ግራ
በኅሊናህ ፋባ  በራስህ ተመራ 
ሁሌም ለወንጌል ቃል ታማኝ ሁን አደራ